ትዕዛዝዎ ደርሶናል | Your order has been received

SHABA CLOSET

ትዕዛዝዎ ደርሶናል!

ትዕዛዝዎን ለማረጋገጥ እንደውልልዎታለን።
ስልክዎን በአቅራቢያዎ ያድርጉ።

50% ቅድመ ክፍያ16–21 ቀናት የማድረሻ ግምት

ዝርዝሩን በጥሪው ወቅት እናረጋግጣለን።

በሻባ ለመጀመሪያ ጊዜ እያዘዙ ነው?

አሰራራችንን ከታች ይመልከቱ። ፎርሙን መሙላት የመጀመሪያው ደረጃ ነው፤ ትዕዛዝዎ በስልክ ይረጋገጣል። ከመክፈልዎ በፊት ዝርዝሩንና የክፍያ መመሪያውን ከቡድናችን ያረጋግጡ።

ቀጣዩ ምንድን ነው?

  1. 01

    ዝርዝሩን እናረጋግጣለን

    ምርቱን፣ ሳይዙን፣ ቀለሙን፣ ዋጋውንና አድራሻዎን በስልክ እናረጋግጣለን።

  2. 02

    የክፍያ መረጃ እንሰጥዎታለን

    ምርቱን፣ ጠቅላላ ዋጋውንና የማድረሻ ጊዜውን ከተስማሙ በኋላ የቅድመ ክፍያ መመሪያ እንሰጥዎታለን።

  3. 03

    ትዕዛዝዎን እናዘጋጃለን

    የማድረሻ ጊዜውን እናሳውቅዎታለን፤ ትዕዛዝዎ ሲደርስም እናነጋግርዎታለን።

ቅድመ ክፍያው የዋጋው አካል ነው።

በአዲስ አበባ፦ 50% በቅድሚያ፣ ቀሪውን 50% እቃው ሲደርስ ይከፍላሉ። ቅድመ ክፍያው ተጨማሪ ክፍያ አይደለም።

ከአዲስ አበባ ውጭ፦ ቀሪው ክፍያና የመላኪያ ክፍያ እቃው ከመላኩ በፊት ይጠናቀቃል።

ለምሳሌ፦ የምርቱ ዋጋ 6,000 ብር ከሆነ፣ 3,000 ብር በቅድሚያ፣ 3,000 ብር ቀሪ ክፍያ ይሆናል። የማድረሻ ክፍያ ካለ ቡድናችን በተለየ ያሳውቅዎታል።

ማድረስ ለምን ጊዜ ይወስዳል?

አንዳንድ ምርቶች በትዕዛዝ ስለሚመጡ፣ ፎርሙን እንደሞሉ ወዲያውኑ አይላኩም።

በድረ ገጻችን የተገለጸው የማድረሻ ግምት 16–21 ቀናት ነው። ትክክለኛው ጊዜ እንደ ምርቱና አካባቢዎ ይለያያል።

ከመክፈልዎ በፊት ለትዕዛዝዎ የሚጠበቀውን ጊዜ ከቡድናችን ያረጋግጡ። ለተወሰነ ቀን ወይም በዓል ከፈለጉት በጥሪው ወቅት ይንገሩን።

ሌላ ጥያቄ አለዎት?

ጥሪው ካመለጠኝ ወይም ስልኬን በስህተት ካስገባሁ?
ከታች ያለውን የቴሌግራም አዝራር ተጭነው ስምዎንና ትክክለኛውን የስልክ ቁጥር ይላኩልን። ለመነጋገር የሚመችዎትን ሰዓትም ይንገሩን። አዲስ ፎርም መሙላት አያስፈልግም።
ከከፈልኩ በኋላ ትዕዛዜን እንዴት ልከታተል?
የክፍያ ማረጋገጫዎን ያስቀምጡ። የትዕዛዝ ቁጥርዎን ካገኙ በኋላ፣ ቁጥሩንና የስልክ ቁጥርዎን በትዕዛዝ መከታተያው ላይ ያስገቡ። ቁጥሩ ከሌለዎት ወይም መረጃው ካልታየ ቡድናችንን ያነጋግሩ።
ሳይዝ ወይም ቀለም መቀየር ብፈልግ?
ቡድናችን ሲደውል የሚፈልጉትን ለውጥ ይንገሩን። ስለ ሳይዝ ካልተረጋገጡም እንረዳዎታለን። ለተመሳሳይ ትዕዛዝ ፎርሙን ደግመው መሙላት አያስፈልግም።
እቃው ሲደርስ ሳይዙ ትክክል ካልሆነ?
በተቻለ ፍጥነት ቡድናችንን ያነጋግሩ። የሳይዝ መቀየር በሚገኝ ሳይዝና በምርቱ ደንብ ይወሰናል። ከማዘዝዎ በፊት የመመለሻና የመቀየሪያ ደንባችንን ይመልከቱ፣ ወይም በጥሪው ወቅት ይጠይቁን።

ትዕዛዝዎ ተመዝግቧል። ፎርሙን ደግመው መሙላት አያስፈልግም።