Frequently Asked Questions
Shaba Closet Support
ጥያቄዎችዎ መልስ አላቸው።
ስለ ማዘዝ፣ ክፍያ፣ ሳይዝ፣ ማድረስ እና መቀየር ማወቅ የሚፈልጉት ቀላል መልሶች። Clear answers about ordering, payment, sizing, delivery and exchanges.
ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
አማርኛእንዴት ማዘዝ እችላለሁ?
የፈለጉትን ምርት፣ ሳይዝና ቀለም ይምረጡ፤ ከዚያ የትዕዛዝ ፎርሙን ይሙሉ። ቡድናችን ደውሎ ዝርዝሩን ካረጋገጠ በኋላ ትዕዛዝዎ ይዘጋጃል።
ክፍያው እንዴት ነው?
በአዲስ አበባ 50% ሲያዙ እና ቀሪውን 50% እቃው ሲደርስ ይከፍላሉ። ከአዲስ አበባ ውጭ ቀሪው ክፍያና የፖስታ ወይም የማድረሻ ክፍያ ከመላኩ በፊት ይጠናቀቃል።
ማድረሱ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
የማድረሻ ጊዜው እንደ ምርቱና አካባቢዎ ይለያያል። ትዕዛዝዎን ስናረጋግጥ የሚጠበቀውን የማድረሻ ጊዜ እንነግርዎታለን። በእጅ ያሉ የተመረጡ ምርቶች በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ሊደርሱ ይችላሉ።
ከአዲስ አበባ ውጭ ታደርሳላችሁ?
አዎ። በፖስታና በማድረሻ አጋሮች ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች እንልካለን። የመላኪያ ዘዴና ክፍያው ከመላኩ በፊት ይረጋገጣል።
ትክክለኛውን ሳይዝ እንዴት ልምረጥ?
በምርቱ ገጽ ያለውን የሳይዝ መመሪያ ይመልከቱ። ካልተረጋገጡ ቁመትዎን፣ ክብደትዎን፣ በተለምዶ የሚለብሱትን ሳይዝና የሚፈልጉትን አቀማመጥ ይላኩልን።
ሳይዙ ትክክል ካልሆነ መቀየር እችላለሁ?
እቃውን እንደተቀበሉ በተቻለ ፍጥነት ያነጋግሩን። መቀየር በእቃው ሁኔታ፣ በሚገኝ ሳይዝና በምርቱ ደንብ ይወሰናል።
ካዘዝኩ በኋላ ትዕዛዜን መቀየር እችላለሁ?
የትዕዛዝ ቁጥርዎን ይዘው ወዲያውኑ ይደውሉ ወይም መልዕክት ይላኩ። ትዕዛዙ ከመዘጋጀቱ ወይም ከመላኩ በፊት ሳይዝ፣ ቀለም፣ አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ለመቀየር እንሞክራለን።
ትዕዛዜን እንዴት ልከታተል?
የትዕዛዝ ቁጥርዎንና የስልክ ቁጥርዎን በትዕዛዝ መከታተያ ገጽ ላይ ያስገቡ።
ምርቱ በፎቶው እንዳለው ነው?
ምርቶቹን በተቻለ መጠን ትክክለኛ እናሳያለን። በብርሃንና በስክሪን ምክንያት ቀለም ትንሽ ሊለያይ ይችላል። የምርቱ ዝርዝር ከመግዛትዎ በፊት ይረጋገጣል።
ድረ ገጹ ላይ የሌለ እቃ ፈልጋችሁ ታገኙልኛላችሁ?
አዎ። ፎቶ ወይም ዝርዝር መግለጫ ከሚፈልጉት ሳይዝ፣ ቀለምና በጀት ጋር ይላኩልን፤ ተመሳሳይ አማራጮችን ፈልገን እናሳይዎታለን።
Frequently asked questions
EnglishHow do I place an order?
Choose your item, size and colour, then complete the order form. Our team will call to confirm the details before preparing your order.
How does payment work?
For Addis Ababa orders, pay 50% when ordering and the remaining 50% when your order arrives. Outside Addis, the balance and postal or delivery fee are completed before dispatch.
How long does delivery take?
Delivery time depends on the product and your location. We confirm the expected delivery window with you. Selected in-stock Addis items may arrive within 24 hours.
Do you deliver outside Addis Ababa?
Yes. We send orders to cities across Ethiopia through postal and delivery partners. The method and fee are confirmed before dispatch.
How do I choose my size?
Check the size guide on the product page. If you are unsure, send your height, weight, usual size and preferred fit so our team can recommend the closest size.
Can I exchange an item if the size is wrong?
Contact us as soon as possible after receiving it. Exchanges depend on the item’s condition, available size and product terms.
Can I change my order after placing it?
Call or message us immediately with your order number. We can try to change the size, colour, address or phone number before preparation or dispatch.
How can I track my order?
Enter your order number and phone number on the Track your order page.
Is the product exactly like the photo?
We show products as accurately as possible. Colours can vary slightly because of lighting and screen settings. Product details are confirmed before purchase.
Can you find an item that is not on the website?
Yes. Send a photo or description with your preferred size, colour and budget. We will search and send suitable options.
አሁንም እርዳታ ይፈልጋሉ?
Send us your order number and our team will help you.